BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
በድሬዳዋ ከተማ ጉዳይ ላይ በሀገራዊ ምክክሩ ከምን ስምምነት ላይ ተደረሰ?
በሀገራዊው ምክክር ላይ የድሬዳዋ ከተማ በፌዴራል ከተሞች ጉዳይ ስር ምክክር ከተደረገባቸው ሁለት ከተሞች አንዱ ነው። ከኦሮሚያ እና ከሶማሌ ክልሎች በተወከሉ የምክክሩ አባላት መካከል ከፍተኛ የይገባኛል ክርክር እንደተደረገባት በምክክሩ ላይ የተሳተፉ ታማኝ ምንጭ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ የአዲስ አበባ ከተማ ጉዳይ ሰፊ መነጋገሪያ መሆኑ፣ የድሬዳዋ ጉዳይ ብዙም ትኩረት እንዳያገኝ አድርጎታል። ለመሆኑ በድሬዳዋ ላይ ምን ዓይነት ስምምነት ተደረሰ?
አብን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሁለት ኮሚሽነሮች በጉባዔው አጀንዳዎች ላይ እጃቸውን ለማስገባት ሞክረዋል ሲል ከሰሰ
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሁለት ኮሚሽነሮች በምክክር ጉባዔው አጀንዳዎች ላይ በቀጥታ እጃቸውን በማስገባት ተጽዕኖ ለማድረግ ሞክረዋል ሲል ከሰሰ። ፓርቲው በመግለጫው ሁለቱ ኮሚሽነሮች "በተለይም በከተሞች አጀንዳ ውስጥ" እጃቸውን ማስገባታቸውን ጠቅሶ፣ "የተሳታፊዎችን ፍላጎት ለማስቀየር እና ተጽዕኖ ለማሳደር" ሙከራ ማድረጋቸውን በተደጋጋሚ መታዘቡን አመልክቷል።
ቀጥታ, ትራምፕ አጋራቸው የሆነችው ኦማንን ለኢራን ስምምነት “እንቅፋት ከሆነች” እንደሚደበድቡ አስጠነቀቁ
ትራምፕ የአሜሪካ አጋር የሆነችው ኦማን ከኢራን ጋር ባለው ንግግር ጣልቃ የምትገባ ከሆነ እንደሚደበድቡ መዛታቸውን ፎክስ ኒውስ ዘገበ። አሜሪካ እና ኦማን የሆርሙዝ ወሽመጥን ለማስከፈት ከቴህራን ጋር በተናጠል እየተደራደሩ ነው።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አብን በምክክሩ ሂደት ላይ የደረሰበትን ድምዳሜ እንደማይቀበለው ገለጸ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ በምክክሩ ሂደት ላይ "ከተራ የአሠራር ግድፈት" የዘለሉ "ተደጋጋሚ እና የተደራጁ ጥፋቶች ተፈጽመዋል" ሲል ያቀረበውን ክስ ውድቅ አደረገ። አብን ቅዳሜ ነሐሴ 09/2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ በሀገራዊ ምክክሩ "ገዢው አካል መዋቅራዊ ጥሰቶችን" እንደፈጸመ በመጥቀስ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ "የከተማዋ ነዋሪዎች ድምፅ እና ፍላጎት በአግባቡ ሳይወከል" ታልፏል ብሎ ነበር።
ቢቢሲ አማርኛ በቲክቶክ
አስተማማኝ ዜና እና መረጃን ቅድሚያ ለማግኘት ቢቢሲ አማርኛን ቲክቶክ ላይ ይከተሉ
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች
ቪዲዮ, “ጦርነት ከተጀመረ መንግሥታት ይለወጣሉ፤ ድንበሮች ይቀየራሉ”
ቢቢሲ በኢትዮጵያ እና በቀጣናዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጓል። የኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ፣ ከህወሓት ጋር ያለው ውዝግብ፣ የባሕር በር ጥያቄ እና የቀጠናዊ የጦርነት ስጋቶች በቃለ መጠይቁ ተዳሰዋል። በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ጦርነት ከተጀመረ ውጤቱ መሠረታዊ ለውጥን የሚያስከትል ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።
ቪዲዮ, ኢትዮጵያዊው የማይክሮሶፍት ባለሙያ ስለኤአይ ጥቅም እና ጉዳት ምን ይላሉ?
ዓለማችንን በማይታመን ፍጥነት እየለወጠ ያለውን ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) በአግባቡ መገንዘብ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ እየሆነ የመጣ ይመስላል። ስለ ሰው ሠራሽ አስተውሎት የተዛቡ ምልከታዎች ምንድን ናቸው? ለወደፊቱ የኤአይ ዓለም እንዴት እራሳችንን ማዘጋጀት እንችላለን? የሚሉና ተያያዥ ጥያቄዎችን በተመለከተ ኢትዮጵያዊው የማይክሮሶፍት ባለሙያ ዶ/ር ግርማው አበበ ታደሰ ምላሽ ሰጥቷል።
ቪዲዮ, ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስለምርጫ፤ ስለፕሪቶሪያ፤ ስለአርሲ. . . ምን አሉ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሰናባቹ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ የተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮችን አንስተዋል። ቢቢሲ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ውስጥ አምስት ዋና ዋና ጉዳዮችን መርጦ አውጥቷል።
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
አነጋጋሪ ጉዳይ
በተስፋ ማጣት እና በሞት መሀል፡ የአማራ ክልል ሦስት የጦርነት ዓመታት
በአማራ ክልል ላለፉት ሦስት ዓመታት በፋኖ ኃይሎች እና በመንግሥት መካከል የሚካሄደው ግጭት የበርካቶችን ሕይወት ቀጥፏል፤ ከፍተኛ ሰብኣዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ውድመትም አድርሷል። ቢቢሲ አማርኛ ያነጋገራቸው የክልሉ ነዋሪዎች ከፍርድ ውጭ ግድያዎችን ጨምሮ ንጹኃን እስር እና እንግልትን እያስተናገዱ መሆኑን ይናገራሉ። የትጥቅ ግጭቶችን የሚመዘግበው አክሌድ ከጥር እስከ ሐምሌ 2018 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜውስት ብቻ ከስምንት ሚሊዮን በላይ ሰዎች 'ለግጭት' ተጋልጠዋል ብሏል። ቢቢሲ በግጭቱ በቀጥታ የተጎዱ ነዋሪዎችን እንዲሁም ባለሙያዎችን አነጋግሮ ቀጣዩን ዘገባ አሰናድቷል።
እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚወጣባቸው ግዙፍ የሽምግልና አበባዎች፡ የአበባ አብዮት ወይስ የባህል ለውጥ?
ከጋብቻ በፊት የሚደረገው የሽምግልና ሥነ ሥርዓት ከፍተኛ ድግስ እና ገንዘብ የሚፈስበት እየሆነ መጥቷል። ከሚዘጋጀው ድል ያለ ድግስ ባሻገር በመቶ ሺዎች ብር የሚያስወጡ ቄንጠኛ ግዙፍ የአበባ ‘እቅፎች’ ደግሞ የሽምግልናው ሥርዓት አካል ሆነዋል። በተለይ የሚቀርበው የአበባ ስጦታ መነጋገሪያ ሆኗል። የሽምግልና ሥነ ሥርዓት የሰርግን ቦታ እየተካ ነው? ግዙፉ የአበባ ስጦታስ ከየት የመጣ ልማድ ነው?
"አዲስ አበባ እንደ እንግዳ ካልሆነ ከዚህ በኋላ ለመኖር የምመጣ አይመስለኝም"
የሥዕል እና የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያ የሆነው ዮናስ መኳንንት፤ ተወልዶ ያደገባትን፣ የእንጀራ ገመዱ የነበረችውን አዲስ አበባን ጥሎ ገጠር ከገባ ከጥቂት ወራት በኋላ ሁለት ዓመት ይሞላዋል። "እኔ እዚህ ከመጣሁ ትልቅ እረፍት ነው የሚሰማኝ። በጣም ሰላማዊ ቦታ ነው፤ ምንም ዓይነት የመኪና ድምጽ የለም፣ የምትሰማው የእንስሳት ድምጽ ብቻ ነው" ይላል።
በዘውዱ ሃፍቱ ግድያ የዕድሜ ልክ እስር የተፈረደባቸው ግለሰቦች እንዴት በነጻ እንዲሰናበቱ ተወሰነ?
ከሦስት ዓመት በፊት በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ በአሰቃቂ ሁኔታ በተገደለችው ዘውዱ ሃፍቱ ግድያ ተጠርጥረው የዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተላልፎባቸው የነበሩት ሁለት ፍርደኞች በነጻ እንዲሰናበቱ ተወስኗል። ውሳኔው በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ ከፍተኛ ነቀፌታ ገጥሞታል። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይም ቁጣቸውን ገልጸዋል።
አሜሪካ ከኤርትራ ጋር ምሥጢራዊ ግንኙነት እያደረገች ነው መባሉን አስተባበለች
አሜሪካ አንድ የአፍሪካ ቀንድ አገርን በተመለከተ ከኤርትራ ጋር ድርድር እያደረገች ወይም ምሥጢራዊ ስምምነት ለመድረስ እየሞከረች ነው መባሉን የፕሬዝዳንት ትራምፕ ከፍተኛ አማካሪ ማሳድ ቡሎስ አስተባበሉ። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የአረብ እና የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ ማሳድረ ቡሎስ በኤክስ የማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ አሜሪካ ከኤርትራ ጋር በመሆን በየትኛውም የቀጣናው አገር ላይ እንደማታሴር ገልጸዋል።
አሜሪካ ከኢትዮጵያ እና ከሌሎች የአፍሪካ አገራት የምትፈልጋቸው የጤና መረጃዎች ምንድን ናቸው? ከሉዓላዊነት ጋርስ ምን ያገናኘዋል?
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሥልጣን ከተመለሱ እና ግዙፉን የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት ካፈረሱ በኋላ ለአፍሪካ አገራት የምትሰጠውን ድጋፍ አካሄድ ቀይራለች። ለዚህ ደግሞ ተቃውሞ እና ጥያቄ ያስነሳው ኢትዮጵያን ጨምሮ ከበርካታ የአፍሪካ አገራት ጋር የተፈራረመችው የጤና መረጃ ስምምነት ተጠቃሽ ነው።
በኢትዮጵያ ለኤል ኒኖ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች የትኞቹ ናቸው? ምን ያህልስ አሳሳቢ ነው?
በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከመጠን ያለፈ ዝናብ እንዲሁም ዝናብ በወቅቱ አለመጣሉ ጉዳት አስከትሏል። ዘንድሮም አነስተኛ እና ከልክ ያለፈ ዝናብ ከፍተኛ ስጋት መደቀኑን የሚጠቁሙ ሪፖርቶች እየወጡ ነው። ለመሆኑ የኤል ኒኖ ስጋት ያለባቸው አካባቢዎች የትኞቹ ናቸው? ሁኔታው ምን ያህል አስጊ ነው?
ኤአይ 'በረከት ወይስ መርገምት?' እንዴት እንጠቀመው? ኢትዮጵያዊው የማይክሮሶፍት ባለሙያ ምን ይመክራል?
ዓለማችንን በማይታመን ፍጥነት እየለወጠ ያለውን ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) በአግባቡ መገንዘብ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ እየሆነ የመጣ ይመስላል። ስለ ሰው ሠራሽ አስተውሎት የተዛቡ ምልከታዎች ምንድን ናቸው? ለወደፊቱ የኤአይ ዓለም እንዴት እራሳችንን ማዘጋጀት እንችላለን? የሚሉና ተያያዥ ጥያቄዎችን አንስተን ኢትዮጵያዊ የዘርፉ ባለሙያን አነጋግረናል።
ለአራት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ምድር ስለመኖሩ ቁርጡ ያልታወቀው አውራሪስ
በተለያዩ ምክንያቶች በርካታ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት የመጥፋት አደጋ እንደተጋረጠባቸው ሲነገር ቆይቷል። ከእነዚህ መካከልም አውራሪስ አንዱ ነው ቢባልም ባለፉት አስርት ዓመታት ግን አንስሳው ስለመኖሩ በተጨባጭ የሚታወቅ ነገር እንደሌለ ባለሙያዎች ይናገራሉ። አውራሪስ ከኢትዮጵያ ጠፍቷል? የዱር እንስሳው ስለመኖሩ ወይም ስለመጥፋቱ ለምን ቁርጥ ያለ ነገር ለማወቅ ሳይቻል ቀረ?
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ቀጣናዊ ፖሊሲ የለወጠው የኢራን ጦርነት
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ባላት ግንኙነት የተነሳ የኢራን ዋነኛ ዒላማ ከሆነች በኋላ በቀጣናው አገራት ላይ ያላት መተማመን እየቀነሰች ነው። ለፖለቲካ፣ ለምጣኔ ሃብት እና ሌሎች ፍላጎቷን ለማሟላት ከቀጣናው ውጭ መመልከትን መርጣለች። ለዚህም ከሕንድ፣ ከዩክሬን፣ ከግሪክ፣ ከቆጵሮስ እና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትስስር እያጠናከረች ነው።
በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የአሜሪካንን ባሕር ኃይል እየፈተኑ ያሉት የኢራን ትናንሽ ጀልባዎች
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራንን ባሕር ኃይል እንዳወደሙ ቢናገሩም፣ ኢራን ትናንሽ ፈጣን ጀልባዎችን በመጠቀም በሆርሙዝ ወሽመጥ የመርከቦችን እንቅስቃሴን መግታት ችላለች። ስለእነዚህ ውጤታማ የኢራን ፈጣን ወታደራዊ ጀልባዎች ምን እናውያለን?
መሪዎቹ እየተገደሉበት ባለበት ጸንቶ የቀጠለው የኢራን የጦርነት ወቅት አመራር የተዋቀረው እንዴት ነው?
ኢራን በአሜሪካ እና በእስራኤል እየተፈጸመባት ባለው ጥቃት ከጠቅላይ መሪዋ ከአያቶላህ አሊ ኻሜኒ ጀምሮ በርካታ ቁልፍ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ መሪዎቿ ተገድለውባታል። ነገር ግን አመራሯ ሳይፈረካከስ እየተተካካ ፍልሚያውን ቀጥሏል። ለመሆኑ የኢራን አመራር በዚህ ጦርነት ውስጥ ባለበት ጸንቶ እንዴት ሊቀጥል ቻለ?
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!
ከየፈርጁ
"አዳም አንድ ደራሲ የሚያስፈልጉት ሁሉም ግብዓቶች ተሟልተው ያሉት ፀሐፊ ነው"
የአዳም ረታ አዲሱ 'መዝሙረ ሄላም' የተሰኘው የረዥም ልብ ወለድ መጽሐፍ 1,008 ገጾች ሲኖሩት በአምስት ክፍሎች የተከፈለ ነው። ይህ የአዳም አዲስ መጽሐፍ ከዚህ ቀደም የሚጠቀማቸው እንደ ሕፅናዊነት ያሉ ሥነ ጽሑፋዊ ቴክኒኮችን የያዘ መሆኑን በመጽሐፉ አርትኦት ላይ የተሳተፈው ቢኒያም አቡራ ለቢቢሲ ተናግሯል። የመጽሐፉ መቼት ከዚህ ቀደም እንደነበሩ የደራሲው ሥራዎች ከ1950ዎቹ ማለቂያ እስከ 70ዎቹ መጨረሻ ያሉ ናቸው። መጽሐፉ መጠሪያ የሆነችው ሄላም ከዋና ገጸባሕሪያቱ አንዷ ስትሆን በሁሉም ክፍል ውስጥ ትገኛለች። ለሕፅናዊነት አጻጻፉ ኹነኛ ማስተሳሰሪያ በመሆን ታገለግላለች። ቢቢሲ ከአርታኢው ቢኒያም ጋር ያደረገውን ቆይታ እነሆ. . .
ሙዚቃ በሱቅ፣ በወጥ ቤት፣ በወፍጮ ቤት፣ በጋራዥ. . . የሚያጫውቱት ዲጄዎች
ዲጄ ሲባል መጀመሪያ የሚመጣልን ምሥል ምናልባትም የዳንስ ወለል ላይ ወዝ ወዝ የሚሉ ሰዎች እና ብልጭ ድርግም የሚል መብራት ይሆናል። እነዚህ ዲጄዎች ግን ማንኛውንም ቦታ ለሙዚቃቸው መዳረሻ ማድረግ የሚችሉ ናቸው። ጋራዥ፣ ቴአትር ቤት፣ ፀጉር ቤት፣ መጻሕፍት መደብር፣ ልብስ ሰፊ ቤት፣ ግንባታው ያልተጠናቀቀ 40/60፣ ሸክላ ሠሪ ቤት፣ ወፍጮ ቤት፣ ውይይት ታክሲ. . . የማይገቡበት የለም።
አጃኢብ!
የተመለሱ ጥያቄዎች
ያለባቸው የጤና ችግር ሕክምና እንዲያጠኑ ያደረጋቸው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች
በረከት በቀለ፣ ኪምቢፊዳ በሚል ስም ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ይታወቃል። ወደ ቲክቶክ ብቅ ከማለቱ አስቀድሞ "በስፓይና ቢፊዳ (spina befida) የተያዝኩ ብቸኛው ሰው እኔ ብቻ እንደሆንኩ ይሰማኝ ነበር" ይላል። የአሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት መሥራቹ ዶ/ር ነቢያት ተስፋዬም ልክ እንደ በረከት ሁሉ ከስፓይና ቢፊዳ (የነርቭ ዘንግ ክፍተት) ጋር ነው የተወለደው። አሁን 33 ዓመት እንደሆነው የሚናገረው ዶ/ር ነቢያት፣ በተወለደ በ22ኛው ቀን የስፓይና ቢፊዳ የቀዶ ሕክምና ተደርጎለታል። ሁለቱም ወጣቶች ከራሳቸው ህመም ተነስተው ሕክምና ለማጥናት መወሰናቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

































































































